አንዳንድ ጊዜ ከራሴ ጋር ስሆን አስባለሁ... እሳቸው በነበሩበት ዘመን ብፈጠር ኖሮ ምን ያህል እድለኛ እሆን ነበር? ጫማቸውን በተሸከምኩ፣ በሚሄዱበት መንገድ ላይ ያለውን እሾህ በጠረግኩ፣ ሰዎች በጠሏቸው እና ባገደሏቸው ጊዜ ከጎናቸው ሆኜ ባፅናናኋቸው እላለሁ። በእንባ ታጅቤ "ያ ረሱለላህ፣ ነፍሴ ለእርስዎ ፊዳ ትሁን!" ብዬ ፊት ለፊታቸው በቆምኩ እላለሁ። ነገር ግን የአላህ ውሳኔ ሆኖ እሳቸውን በዚች ምድር ላይ ማየት አልታደልንም። ይህ እውነታ ልብን ይሰብራል፣ ዓይንን በእንባ ያጠባል